
በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሰላም አስከባሪ ማሰልጠኛ ማዕከል የሚቋቋምበት ስምምነት ነገ እንደሚፈረም በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ አስታወቀ።
ኤምባሲው እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ መንግሥትና በተባበሩት መንግሥታት የልማት ድርጅት መካከል የሚፈረመው ስምምነት 14 ነጥብ 77 ሚሊዮን ዶላር ይፈጃል።
በጃፓን መንግሥት በሚገኝ ድጋፍ የሚመሰረተው ማዕከል በዋነኝነት ፕሮጀክቶች ይኖሩታል።
የመጀመሪያው የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ ይኖሩታል፡፡ሁለተኛው በሰላም ማስከበር ላይ ያተኮሩ ግጭቶችን መከላከልና ድህረ-ግጭት የግንባታ ሥራዎች ይከናወኑበታል።
በስምምነቱ ፊርማ ሥነ ሥርዓት ላይ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አህመድ ሺዴ፣ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሂሮዩኪ ኪሺኖ፣የኢትዮጵያ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ማዕከል ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ሐሰን ኢብራሂምና የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተጠሪ ዶክተር ሳሙኤል ብዋሊያ ይካፈላሉ።
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች እያደረገች ባለችው ተሳትፎ እያደገ መጥቷል።በአሁኑ ወቅት በዓለም በአራተኛ በአፍሪካ ደግሞ በመጀመሪያ ደረጃ የሚያስቀምጣት ተልዕኮዎችን አሰማርታለች።
Source: erta
በጣም ደስ ይላል። እናመሰግናለን እንደዚ አይነት ዜናዎች ስላካፈልከን፣ ቀጥልበት።