The CEO of Maichew hospital is accused of rape and sexual harassment on 14 women. The first case of the scandal surfaced after an article by Save Tigray Adna.
Ethiopia’s current Minister of Health, Dr.Kesste Admassu commented on the case on his twitter account (@KeseteA) and asked blogger Daniel Berhane to update him on the case.
We are confused by the poor handling of the Maichew Hospital sexual scandal. Would you take a look & update us? Thanx
Below you will find the details of the sexual scandal.
Daneil Berhane’s Facebook page.
Here is a follow-up post on the @Maichew Hospital scandal that I told you the other day. I can not confirm all the details written below by Save Tigray Adna.
But, I learnt from reliable sources that:
1/ In the weekends, the CEO entered to his office – breaking the seal on his office door. And, he was removed from the hospital compound by security officers.
2/One of the accusations against the guy is an attempt of rape and one of the victims is a nurse.
3/No one bothered to check if female patients of the hospitals have compliants.
4/The deputy mayor of Maichew attempted to get the suspended CEO back to work.
5/The Chief administrator of the zone is out of the country and his return is expected for a final decision on the matter.
The officials in Mek’ele have no time for this – doing God knows what!
Save Tigray Adna
ስልጣን እንደሀሺሽ፤ የሆስፒታሉ CEO፡
በ8 ወር የስልጣን ቆይታው 14 ሴቶችን ስልጣኑን መከታ በመድረግ ፆታዊ ጥቃት ያደረሰው የማይጨው ሆስፒታል ዋና ስራ ኣስኪያጅ( CEO) ከአምስት ቀናት በፊት( በባለፈው እሮብ) በሀኪሞችና ሰራተኞች ከፍተኛ ተቃውሞ ከስራው እንዲታገድ ተደርጓል፡፡
አቶ ብርሀኑ ይባላል፡፡ እንደብዙዎቹ የክልሉ የሆስፒታሎች ስራ-አስኪያጅ በተፋጠነ የኤች .ኦ(Accelerated Health Officer) በ1 ዓመት ከምናምን ትምህርት ጤና መኮንነት የተሰጠው ነው፡፡ ከዚህ በፊት “ዐዲሹሁ” በተባለ ጤና-ጣብያ ስራ-አስኪያጅ ሁኖ ሰርቷል፡፡ እዛ በሚሰራበት ጊዜም ብዙ ተመሳሳይ ሀሜቶች ይሰሙ ነበር፡፡ ብዙ ሴት ሰራተኞች ላይ ስልጣኑን መከታ በማድረግ ፆታዊ ጥቃት እንዳደረሰ ብዙ ሀሜቶች እንደነበሩ ተሰምቷል፡፡ ሌላ ቀርቶ ለኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ድርጅታዊ ስልጠና ጦላይ በሄደበት ወቅትም አንድን ሰልጣኝ ሴት ደፍሮ በእርቅ እንዳለቀ ተሰምቷል፡፡
ይህ የአስገድዶ መድፈር ሱሰኛ የማይጨው ሆስፒታል ሐላፊ ሁኖ የተሸመው የዛሬ 8 ወር አካባቢ ነው፡፡
አቶ ብርሀኑ ሆስፒታሉን እግሩ ከረገጠበት ጊዜ አንስቶ የሆስፒታሉ ሰራተኞችን ሲሆንለት እያባበለ፣ አንዳንዴም ስልጣኑን በመመካት እያስፈራራ እስካሁን በውል የታወቁ 14 ሰራተኞችን ፆታዊ ጥቃት አድርጓል ተብሏል፡፡ ከዚሁ ውስጥ አንዷን ነርስ በጉልበት በቢሮው ቆልፎ እንደደፈራት ተሰምቷል፡፡
በፖለቲካዊ ታማኝነት መስፈርት የሚሾሙ ፍፁማዊ የሆነ ስልጣን የተሰጣቸው የሆስፒታል CEOዎች በተለይ በዚህ ክልል የጤና ሴክተሩን ያቀጨጨና ትልልቅ ባለሙያዎችንም ፈፅሞ ከሃላፊነት እንዲርቁና ባለው እንዲህ ዓይነቱ ምግባረ-ብልሹትና የአሰራር ግድፈቶች ሙያቸውን በተገቢ እንዳይተገብሩ ገድቧቸው እንዳለ ከብዙ ከፍተኛ ሐኪሞች በተደጋጋሚ የሚሰማ ነው፡፡ ይህ አሁን የምናወራበት ጉዳይም አንድ ማሳያ ሁኖ ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡
እንደማንኛውም ሆስፒታል በሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር የሚመራ የስልጠና ኮሚቴ ነበር፡፡ ሰውየው ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ይሀንን ኮሚቴ አፍርሶ ስልጣኑን ለራሱ ይዞታል፡፡ ስልጠና በመጣ ቁጥር ማንንም ሳያማክርና ያለወረፋቸውን የፈለጋትን ሴት ሰራተኛ እየመረጠ ለስልጠናዎች እየላከ ለዋለላቸው ውለታም በገላቸውን እንዲመልሱለት ማስገደድ፣ ማባበል ዋና መለያ ባህርይው ሁኖና ብዙ የውስጥለውስጥ ሹክሹክታዎች እያስተናገደና ሆስፒታሉ እየታመሰ ቆይቷል፡፡
ይህ ስራ-አስኪያጅ የሆስፒታሉን መንፈስ አደፈረሰው፡፡ ከሰራተኛው ሁሉ መናጨት ጀመረ፡፡ የሀኪሞችም ስራ ማስተጓጎል ስራው አደረገው፡፡ የወረዳውና የዞኑ ሐላፊዎች እንዲሁም የሆስፒታሉ አመራር ቦርድ በሆስፒታሉ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ቢሰማም እርምጃ ለመውሰድ ግን ዳተኛ ነበር፡፡
ነገሮች በዚሁ እየቀጠሉ ባለበት ሁኔታ አሁንም እንደሁልጊዜው የ1 ወር ሞያዊ ስልጠኛ ዕድል ይመጣና አንድን የሆስፒታሉ ነርስን ማንንም ሳያሳውቅ ይልካታል፡፡ የ1 ወር ስልጠና ጨርሰች፡፡ ስልክ ደውሎም “ግድየለም ስልጠና ላይ ስትደክሚ ስለነበርሽ አንድ ሳምንት አርፈሽ ነይ: በኔ ይሁንብሽ” ይላታል፡፡
ተመልሳ ስራ የጀመረች ቀን እንደለመደው ያንን ውለታውን በገላዋ እነድትመልስ ይጠይቃታል፡፡ ይበልጥ የሚገርመው እቺ ሰራተኛ ባለትዳርና የልጆች እናት ናት፡፡ አልተስማማችም፡፡ “አለዚያ አንድ ሳምንት ያለፍቃድ አሳልፋ መጣች” ብየ እቀጣሻለሁ ብሎ ማስፈራራት፡፡ ወይ ፍንክች፡፡ በዚህ ሁኔታ ነገሩ ይፋ ተሰማ፡፡ አንድ ሁለት እያሉ በፍርሀት ጉዳቸውን አፍነው ዝም ያሉት ሌሎች ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችም እየተግተለተሉ በግልፅ መውጣት ጀመሩ፡፡ 14 ደረሱ፡፡
የሆስፒታሉ 6 ሓኪሞች፣ ጥቃቱ የደረሰባቸው ሴቶች አንድ ላይ ሁነው የሆስፒታሉን የበላይ አመራር ቦርድና
የዞኑ አስተዳዳር እንዲያነጋግራቸው ጠሩ፡፡
ይህ ጉዳይም ይፋ ወጣ፡፡
ታድያ የሚገርመው ቦርዱ፡ “ይህ ሰው ለረዥም ጊዜ ታማኝ የፓርቲው ነባር አባል እንደሆነ ነው መንግስት የሚያውቀው፡፡ እኛ አሁን እርምጃ ለመውሰድ ይከብደናል፡፡ ስለዚህ ነገሩ በደምብ እስቲጣራ በቦታው ይቆይ፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሐይሌ አስፍሀ ለስራ ወደ ውጪ ስለሄዲ ሲመለሱ እርምጃ ይወስዱበታል” ብሎ ምላሹን ሰጠ፡፡
ሓኪሞቹና ተበዳዮቹ ክፉኛ ተቆጡ፡፡ በዚሁ ሁኔታ ወደ ስራ እንደማይመለሱ በየቀኑ የሴት ልጅ በሚደፈርበት ሆስፒታል ሊሰሩ እንደማይችሉና ዛሬውኑ እንደሚለቁ አስረግጠው ተናገሩ፡፡
ቦርዱም አማራጭ በማጣት ያለፈው እሮብ ቀን(ከ5 ቀን በፊት) ከስራው ታግዶ እነዲቆይ አድርጓል፡፡
የተበደሉትንም ሴት ሰራተኞችም “መጀመርያ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበትና ወደ ህጉ ደግሞ ቀጥላችሁ ትሄዳላችሁ” ተብለው እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡
እስካሁን የተመሰረተበት ክስ ግን የለም፡፡
Join Conversations