በአዲስ አበባ የቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ ችግርን ለማቃለል የ26 ተሽከርካሪዎች ርክክብ ተፈፀመ

Is the Ethiopian government fighting corruption hard enough?
Share your thought.
waste treatment in ethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየውን ቆሻሻ አሰባሰብ እና አወጋገድ ችግር ለማቃለል የ26 ተሽከርካሪዎች ርክክብ ተፈፀመ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ በበጀት ዓመቱ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የ80 ተሽከርካሪዎች ግዢ ፈፅሟል፡፡

በሁለተኛ ዙር ወደ ሃገር የገቡት ተሽከርካሪዎች በከተማው ለሚገኙ አስሩም ክፍለ ከተሞች የሚከፋፈሉ ናቸው፡፡

በተጨማሪም ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ የ500 ገንዳዎች ግዥ ፈፅሟል አስተዳደሩ፡፡

የኤጀንሲው ተጠባባቂ ስራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ ስዩም እንደተናገሩት ኤጀንሲው እስከ መጭው አዲስ ዓመት መጀመሪያ ቀሪ 30 የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሽከርካሪዎችና የመንገድ ማፅጃ ማሽነሪዎች ይረከባል፡፡

Source: Erta

Leave a Comment


× five = 15