በውጭ አገራት የሚኖሩ ዜጎች ወደየአገራቸው የሚልኩት ገንዘብ እያደገ መምጣቱን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።
የመንግሥታቱ ድርጅት የዜና ማዕከል ባወጣው ዘገባ በውጭ አገራት የሚኖሩ ዜጎች የሚልኩት የገንዘብ መጠን በዓመት 200 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል፡፡ በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ወደ አገር ቤት የሚልኩት ገንዘብ የገጠሩን ኢኮኖሚ ከመደገፉ ባሻገር በዓመት በአማካይ እስከ 30 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የኢንቨስትመንት ዕድል ሊፈጥር እንደሚችል ዘገባው አመልክቷል።የመንግሥታቱ ድርጅት የግብርና ልማት ዓለም አቀፍ ፈንድ ፕሬዝዳንት ካናዮ ንዋንዚ እንዳሉት ከውጭ ወደ አገር ቤት የሚላከው ገንዘብ በገጠሩ አካባቢ የሚኖረው ህዝብ ከድህነት ለመውጣት የሚያደርገውን ጥረት በማነቃቃት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።ከውጭ የሚላከው ገንዘብ በአስገራሚ መልኩ እያደገ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸው የሚላከውን 200 ቢሊዮን ዶላር በአግባቡ በመቀጠም ለውጥ ለማምጣት ስትራቴጂያዊ መንገዶች መቀየስ እንደሚገባ ተናግረዋል።በዓለም አቀፍ ደረጃ 215 ሚሊዮን ህዝብ ከአገሩ ውጭ የሚኖር ነው።

ምንጭ ፣ ኢዜአ
Join Conversations