በአማራ ክልል በሚገኙ አራት ከተሞች የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሊገነቡ ነው Condominium to be built in four Amhara region cities

Addis Ababa Condominium houseአዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በምሥራቅ አማራ በሚገኙ አራት ከተሞች ከ200 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሊገነቡ ነው ።

የአማራ ክልል ቤቶች ልማት ድርጅት የደሴ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱ ጀማል እንደተናገሩት ፥ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ የሚካሄደው በደሴ ፣ ኮምቦልቻ ፣ ወልድያና ደብረብርሃን ከተሞች ነው።

የቤቶቹን ግንባታ ለመጀመርም ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ ።

ድርጅቱ በከተሞቹ የሚታየውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃላል የሚገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከሰባት እስከ 12 ፎቅ ይኖራቸዋል ።

ድርጅቱ በከተሞቹ ለረጅም ዓመታት አገልግሎት የሰጡ አሮጌ መኖሪያ ቤቶችን በዘመናዊ ሕንጻዎች የመተካት ሥራም እንደሚያከናውን ሃላፊው ተናግረዋል ።

FanaBC

ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።

Leave a Comment


8 − seven =