አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) በምሥራቅ አማራ በሚገኙ አራት ከተሞች ከ200 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሊገነቡ ነው ።
የአማራ ክልል ቤቶች ልማት ድርጅት የደሴ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱ ጀማል እንደተናገሩት ፥ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ የሚካሄደው በደሴ ፣ ኮምቦልቻ ፣ ወልድያና ደብረብርሃን ከተሞች ነው።
የቤቶቹን ግንባታ ለመጀመርም ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ ።
ድርጅቱ በከተሞቹ የሚታየውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃላል የሚገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከሰባት እስከ 12 ፎቅ ይኖራቸዋል ።
ድርጅቱ በከተሞቹ ለረጅም ዓመታት አገልግሎት የሰጡ አሮጌ መኖሪያ ቤቶችን በዘመናዊ ሕንጻዎች የመተካት ሥራም እንደሚያከናውን ሃላፊው ተናግረዋል ።
FanaBC
ትኩስ እና ሰበር ዜና፣ በብዛት የታዩ ቪድዮዎችን፣ ድራማዎችን፣ሙዚቃዎችን እና አስገራሚ ታሪኮችን በኢሜል አድራሻዎ እንልካለን። ኢሜሎን ያስመዘግቡ።
Join Conversations