ስለሞታችሁ ሞቴን አሰብኩ Your death makes me think about my own death

originalስለሞታችሁ ሞቴን አሰብኩ እጅግ ከፍቶኛል እግዚሐብሄር ዛሬም እንደትናንቱ ከእኔ ጋር እንዲኖረ ወደድኩ፡፡ ህትና ወንድሞቼ በመከራ ላይ ሲወድቁ አዩሁ እምባዬም የተፈጥሮ ማዕዘናቸውን ይዘው ወረዱ አንጀቴም ቦተውን ለቆ ሲሰበሰብ አየሁ ለካስ በህይወቴ ከእኔኔቴ በላይ የኖርኩት በኢትዮጲያዊነቴ መሆን የተረዳሁበት ዘመን ቢኖር ይሄ ነው፡፡ እኔ ነቴ በከፉ መሬት በከፉ እጅ አንዲሁም በአረመኔ እግር ስር ሲወድቅ አየሁ፡፡

ጌታዬ ሆይ ስለምን ይሆን ብዬ ጠየኩ ምን አለባት መልስ ለማግኘት ተገቢ ጠያቂ ላልሆን እችላለሁ ምክንያቱም በአምላክ ዘንድ እኔ ቀላል ነኝና፡፡ በዚች ላልተወሰነ ጊዜ ለምንኖርባት ዘመን ስለምን መፈጠራችንን ጠላን በደላችንሰ ምን ይሆን አንዲህ በክፎዎች መደፍ የጣለን፡፡ የወንድሜንና የህቴን አንገት የክብር ቦታውን ስቶ በእምነት ማህተቡ ላይ የህለፈት ዘመኑን የመከራ ጊዜው ያበቃለት ዘንድ ያልተባረከና ያልተቀደሰ ገመድ ተደርቦበት አየሁ፡፡

ኢትዮጲያዊነቴ ከአንግታቸው ጋር ዘነብል አለ ግን የኔ ከደቂቃዎች በሀኃላ ቀና አለ የነሱ ግን እደዚያው ነው፡፡ ምን አልባት እነሱ ከእኔ በላይ አዝነው ይሆን ብዬ ጠበቁ ግን እነሱ ለዘላለም ጎነበስ እንዳሉ ተረዳሁ፡፡ ይቺ አገር የእምነትና የበረከት አገር አንደነበርች ሰማሁ አናም አመንኩ ግን የሚታየው ግን ይህ አለመሆኑን ሳይ ደግሞ በረከታችን ተጀምሮ ሳንደርስበት አልቆ ይሆን ብዬ እጠይቃለሁ፡፡
ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ዝርጋታ ሞዴል ተባለች Ethiopia is model for Africa in Interne…

መከራችን አላበቃም በዚች ያለ አድሎ በተፈጠረች አለም የሰው ልጅ ከፈጣሪዋ በላይ አደላበት እናም የንጸሁን እንባ አንደጅረት ፈሰሰ ከአምላክ ጽዋም በላይ ሆነ በእርግጥ አምላክ ለምን ይህን አደረክ ብለን አንጠይቀውም ምከንያቱም እሱ የኛን መጨረሻ ከእኛ በላይ ያውቀዋልና፡፡

ሁሉም የሰውልጅ አፈር ቢሆኑም አንዱ አፈር ሌላኛው አፈር ላይ የሚደረሰው በደል ግን ከመንጊዜውም በላይ በዚህ ስልጡንና አዋቂ ትውልድ ሲፈጸም የማወቅንና የመስልጠን ትርጓሜን ወደፊት ባሰቡከት መጠን ከበደኝ፡፡በእርግጥ እኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ብሞት አንዳች ፍራቻም ሆነ ቀረብኝ የምለው ነገር የለም ምክንያቱም ለመሞት እኔ ራሴ መሞት የለብኝም እኔነቴ ኢትዮጲያዊነቴ አስቀድሞ ሞቷልና፡፡ ሰው ለምን ክፉ ይሆናል፡፡

በአንድ ወቀት ተቀጥረው በትህተና ይሰሩባት የነበሩባትን አገር ዜጎች ዛሬ ቀን ጥሎአቸው ይኖሩበት ቢከብዳቸው ይዘረጉበት ማዕድ ቢያጥራቸው ጉልበታቸውን አና ማንነታቸውን መንዝረው በንጹህ ትህተና ያረፉባቸው መክዳቸው እሳት ሆኖ ወገኖቻችንን ፈጆቸው፡፡ ደማቸው የእናት ሆድ አጥቶ በማይራራ እጅ ተዳሰሰ አስተውሎ በማይመለከት አይንም ተጎበኝ፡፡

ዋይ ብላ ደረቷን የምትመታ ኩተዋን አንስታ የምትሸፍን ኢትዮጲያዊት እናት በሌለችበት ቦታ የልጇ ደም ፈሶ ግንባሯን ከመሬት ጋር አጣበቀው፡፡ አቤቱ ጌታዬ ሆይ በዚህ ጌዜ አንኳን ቀሻሻውና ደካመው ስጋ ቀርቶ ነፈስ ማረፊዋ የት ይሆን፡፡

እባክህ ስለናትህ አንተ ነህ ትምክህታችን ስለማንነታችን ሳይሆን ስለጌትነትህ ፈረድልን፡፡ ስለኛስ ከሰው ወገን የሚቀረቆርልና የሚያዝንልን ጠፍቷልና፡፡ ስደተቻን በክረምት አይሆን ዘነድ በትመክረንም ዘሬ የደጋግና ፈሪህና አክባሪህ ልጆች በጠራራ ጸሀይ ስደታቸው ከፍቷልና፡፡ ችግር እርግማን አይደለም ከተሳሰቡና ከተባበሩ ግፍትረው የሚጥሉት የአንድነት ስራ ውጤት ነው፡፡ በእርግጥ አብሮ መስራትና ተቀራራቢ ሃሳብን ማመንጨት ካቃጣት ኢትዮጲያ አገሬ ብዙ ዘመናት ያለፋት ይመስላል፡፡

ለመሬትና ቃል ኪዳንን በትታደለም እንደ ተረገመች መሬት ውንድማቾች የአቤልና የቃዬልን ስራ ሰሩ፡፡ ጎታራ ለማይሞላ ትርፍ አልባ መስቅልቅል ተዳረገን እልፍ አላፋት ልጆቿ በየስርቻውና በየዱሩ እና ገደሉ ደሙ ፈሰሰ አናም ሰው ቢኖራትም ያሰተሳሰብ ምንጮቿ አየታደኑ በመጥፋታቸው ጋኖቿ ጠፍተው ምነቸቶች ጋን ሆኑባት፡፡ በእርግጥ ዛሬ በሰው አገር ብቻ አይደለም መከራችንን እያየን ያለነው እዚሁ በቀያችን በገንዛ ወገኖቻችንም ተሰፋችን እዲተን የሚሰራው ሴራ ቀላል አይደለም፡፡ የዚህም ውጤት የዕለት እስትንፋስን ለማራዘም እሾህ ቆንጥሩን ሀሩር በረሃወን እየተንከለከሉ አካለቸው ለእዋይ ለመሰሪ በላቾች የተጋለጠው ሲልፍም የአሳ ነባሪ ቀለብ የሆነው፡፡

ዛሬ ዛሬ አገራችን ተስፋ እንዲኖራት ሰላሟን ጠብቃ አንደ አገር አገር ለመሆን ቀና ደፋ ብትልም የገንዛ ልጆቿ የከፉባት ይመስላል፡፡ አንድ ሰው አስቦ አንድ በሬ ስቦ ይሉት አይነት ሆና ጥቂቶች ጎንበስ ቀና ሲሉ ብዘሁኑ ግን የራሳቸውን ከንቱ አላማ ለማስፈጸም እንቅለፍ አጥተው ያድራሉ፡፡ ያው ቢሞላ ከጥጋብ በላይ ላይሆን እንስሳ እንኳ ከጠገበ በኋላ በማያድንበት በዚህ ምድር እኛ ሰዎች ግን ከእንስሳም በታች ወረደን የራሳቸውን አምሳል ለውርደትና ለሞት ሲዳርጉት የእነሱም እጣፈንታ ከዚያ የተለየ አለመሆኑን የዘነጉት ይመስላል፡፡

እኔ በአገሬ ተሰፋ አልቆርጥም፡፡

እናት ኢትዮጲያ በሰላም ትንሳዬዋ የሚነገርበት ትንቢቷም የሚፈጽመበት የልጆቿ ሀዘን አብቀቶ አንኳን ለራሷ ዜጎች አይደለም ልክ እንደ ጥንቱ ይደርሱበት ለጨነቃቸው መጠለያ የምትሆንበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ በእርግጥ ይህን ስናሰብ እንዲሁ በቀላሉ እንደማይመጣ ልብ ልንል ይገባል ዘመኑ የሚከፈለውን መሰዋትነት አክበዶታልና፡፡ ስለእውነት መቆርቆርና ስለአገር መቆርቆር አንደ ወንጀል እየታየ የራሳቸውን ጠባብ አለማና ከርስ ለመሙላት አገሬ ኢትዮጲያ ከመንጊዜውም በላይ በግለሰቦች ጭቆና የወደቀቸበት ጊዜ ቢኖር ይሄ ጊዜ ነው፡፡

ለስራ መታተርና ዜጋን ለማገልገል ተፍ ተፍ ማለት አንደ ወንጀል ተቆጥሮ የጥቂት ፈላጭ ቆራጭ ግለሰቦችን ሃሰባን አለማሳከት አገርን እደመጉዳት ተቆጥሮ ብርቱዎች በየበረንዳውና ስርቻው እንዲወድቁ አልያም በአድርባይነት ራሰቸውን ለውጠው ከእነርሱነታቸው ይልቅ በነገ ያለፋል ብሂል እስተንፋሰቸውን የምታረዝምላቸውን መንዳ በሰላሳኛው ቀን ይወርድ ዘንድ ይጠብቃሉ በሰላሰኛውም ቀን ዋጋውን ባዩ ጊዜ አንገታቸውን ይደፋሉ፡፡

በእርግጥ ሰው መሆን ለካ አንዲህ ማነስ መሆኑን ሳሰብ ከአምላክ እኩልም ባይሆን እኔም በመፈጠሬ ተጸጸትኩ፡፡ ብቻ ለእኔ ሞታ ትልቁ የአምላክ ቸርነት ነው፡፡ ሞት ግን ሞት የሚሆነው በቁም በውርደት ሲሞቱት ብቻ ነው የሚከፋው፡፡

እናንት ወድ ህትና ወንድሞቼ እንኳን ደግ አደረጋቸሁ ከቁም መከራቸሁ ይልቅ ሞታችሁን ስለመረጣቸሁ፡፡ በእርግጥ ዛሬ አሟሟትን ካልሆነ በቀር ሞትን የሚፈራ ያለ አይመስለኝም፡፡ሌላ ምንም አልልም በምድር ለከፈላችሁት እግዚያበሔር ለቀጣዩ ማንነታቸሁ የቸርነቱን ስራ በእናተ ላይ ይስራ፡፡

እግዚያበሄር ኢትዮጲያን ይባርክ የህትና ወንድሞቻችንም ህይወት እንዲያበቃ ያድርግ፡፡

Leave a Comment


+ three = 8