እንጀራ ሳይሻግት 10 ቀናት ማቆየት ተቻለ | Ethiopian Opinion

እንጀራ ሳይሻግት 10 ቀናት ማቆየት ተቻለ

Would you be willing to use a preservative to keep Enjera fresh?
Share your thought
enjera preservative
እንጀራ ሳይሻግት 10 ቀናት ማቆየት ተቻለ

የኢትዮጵያውያን ባህላዊ ምግብ ሲባል በአብዛኛው ትዝ የሚለን እንጀራ በወጥ ነው። ብዙ ሰዎች “እንጀራ ሳልበላ ሁለት ቀን መቆየት አልችልም” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ለእንጀራ ደንታ የላቸውም፡፡ “ጭድ መብላት ሆድ መሙላት ነው፡፡ እንጀራ ባልበላ ከአይረን (ብረት ማዕድን) በስተቀር ምን ይቀርብኛል? ብረት እንደሆን ከሌላ ምግብ አገኛለሁ” ይላሉ፡፡ እነዚህ የእንጀራ ጥቅምና ምስጢር ያልገባቸው ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ እንጀራ የሕልውና መሠረት ስለሆነ በኅብረተሰቡ ውስጥ ብዙ ባህላዊ አባባሎች አሉት። “እንጀራህ ይባረክ፤ ጥሩ እንጀራ ይስጣችሁ፤ ጥሩ እንጀራ ይውጣልሽ፣ የማታ እንጀራ ይስጥህ፣ ሌማታችሁ በእንጀራ ይሞላ፤ ከሌማትሽ የምትቆርሺው እንጀራ አትጪ፣…” እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እንጀራ፣ ለበርካታ ዘመናት የኅብረተሰቡ ምግብ ሆኖ ቢቆይም በርካታ ችግሮች እንዳሉበት የታወቀ ነው፡፡ ለመሆኑ እንጀራ ሳይሻግት ስንት ቀን ይቆያል? ብልዎት መልስዎ “ሦስት ወይም አራት ቀን” እንደሚሆን አልጠራጠርም፡፡ ቶሎ መሻገቱ ዋነኛ ችግሩ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ በመሻገቱ የተነሳ የሚፈጠረው ብክነት ነው፡፡

የሻገተ እንጀራ ስለማይበላ ይደፋል፤ ባከነ ማለት ነው፡፡ ልጆች ሆነን ታናሽ ወንድሜ የሻገተ እንጀራ ከተሰጠው፤ “ጢም ያወጣ እንጀራ አልበላም” ብሎ የሚያኮርፈው ትዝ ይለኛል፡፡ ዛሬ፣ እንጀራ ስላለው ጠቃሚ ነገሮችና ስለ አንድ የምርምር ውጤት አጫውታችኋለሁ፡፡ ምርምሩ የተካሄደው በአውሮፓ ወይም አሜሪካ አይደለም – እዚሁ በአገራችን ካሉት ቀደምት የትምህርት ተቋማት አንዱ በሆነው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ የጥናቱ ውጤት እንጀራ ሳይሻግት 10 ቀናት ማቆየት የሚያስችል ነው። ውጤቱንም ያገኘው የውጭ ዜጋ አይደለም – ወጣት ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ ነው፡፡ ተመራማው አቶ አሻግሬ ዘውዱ ይባላል። የምርምሩ ውጤት አንቱ የሚያሰኝ ቢሆንም ከዕድሜው ወጣትነት የተነሳ አንተ ልለው ተገድጃለሁ፡፡

አቶ አሻግሬ የተወለደው በአዲስ አበባ ከተማ ነው – በ1973 ዓ.ም፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪውን ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በኬሚስትሪ አግኝቷል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ “ፉድ ሳይንስ ኤንድ ኑትሪሽን ሴንተር” መምህርና ተመራማሪ ነው፡፡ ሁለተኛ ዲግሪውን ያገኘው እንጀራ ሳይሻግት ለብዙ ቀናት ማቆየት በሚቻልበት ዘዴ ላይ ባደረገው ምርምር ነው፡፡ ሦስተኛ ዲግሪውንም በእንጉዳይ ላይ ባደረገው ጥናት ለመያዝ ተቃርቧል፡፡ በእንጀራ ዙሪያ ባደረገው ጥናትና ለወደፊት በምን መልኩ ሊያቀርበው እንዳሰበ ከአቶ አሻግሬ ዘውዱ ጋር ያደረግሁት ቃለ – ምልልስ በዚህ መልኩ ቀርቧል፡፡

Click here to read interview

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *


4 − = one

You may use these HTML tags and attributes: <a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <strike> <strong>