‹‹የኢትዮጵያ ሶማሌ›› “Ethiopian Somali”?

9ባለፈው ሳምንት ‹የኢትዮጵያ ብሄሮችና ብሄረሰቦች ሕዝቦች ቀን› በጅግጅጋ በድምቀት ተከብሯል፡፡ ጥሩ ነው፡፡ አንድ ጥሩ ያልሆነ ነገር ግን ነበር፡፡ በዓሉ በሶማሌ ክልል በመዘጋጀቱ ምክንያት የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ጨምሮ በርካታ ባለስልጣኖችና የሚናገሩትን በቅጡ ያስተዋሉ የማይመስሉትና የገደል ማሚቶነት

99የሚበረታባቸው የመንግስት ጋዜጠኞች ‹‹የኢትዮጵያ ሶማሌ›› የሚለውን ቃል ጆሯችን እስኪደማ ሲያሰሙን ሰንብተዋል፡፡ ለመሆኑ ለምንድነው ‹‹የኢትዮጵያ ሶማሌ›› የምንለው? ለምን ‹‹የኢትዮጵያ አፋር››፣ ‹‹የኢትዮጵያ ኦሮሞ››፣ ወዘተ. የማንለው? ለምንድነው ‹‹የሶማሌ ክልል›› ማለት የማይበቃን? ይህ በሽታ ከቅኝ ግዛት ዘመን የመጣ ነው፡፡ ‹‹የእንግሊዝ ሶማሌ››፣ ‹‹የጣልያን ሶማሌ›› እና ‹‹የፈረንሳይ ሶማሌ›› ሲባል ኖሯል፡፡ የታሪክ ድርሳናትም እንደዚሁ ነው የተመዘገቡት፡፡ እኛም ያንኑ ይዘን ‹‹ከቅርጫው የወስድነውን ድርሻ አትርሱብን›› የምንል እንመስላለን፡፡ ቅኝ ገዢዎች ነን እያልን ነው፡፡ አንደበታችን እናምንበታለን የምንለውን መርህ ይጻረራል፡፡ ድርጊታችንም አንደበታችንን ልከተል ቢል አስገራሚ አይሆንም፡፡ ተግባርን የሚመራው የፖለቲካው መንፈስ ነውና፡፡

Leave a Comment


three × 6 =